ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ

ቦንጋ የትምህርት ኮሌጅ በጀርመን ሀገር በቱሪንግያ ግዛት (Thuringia State) ከሚገኘው ኤርፈርት ዩኒቨርሲቲ (Erfurt University) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የልምድ ልውውጥ እና ውይይት አደረገ።
ኮሌጁ ከዪኒቨርሲቲው በቀረበለት ግብዣ መሰረት በጋር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የቦንጋ ትምህርት ኮሌጅ ዲን አቶ አንተነህ አየለ በቦታው በመገኘት ከዩኒቨርሲትው የስራ ኅላፊዎች፣ Prof. Dr. Sven Jockol, Dean of philosophy faculty. Prof. Dr. Iris Shroder, Director for Transcultural study college እና የስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በመሆኑም በቀጣይ፣
* በመማር ማስተማር ዘርፍ ፣ በሁለቱ ተቋማት የሚገኙ መምህራን እና የትምህርት ባለሙያዎች የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ማማቻቸት፣
* የምርምር ሰራዎችን በትምህር ጥራት፣ በቋንቋ፣ ባህል እና ታሪክ ላይ እንዲሰሩ የመደጋገፍ ፣
* በባህል፣ ቋንቋ እንዲሁም ታሪክ ላይ ጥናት የሚያደርጉ ተመራማሪዎች በኤርፈርት ዩኒቨርሲቲ ስር የሚገኘውን እና በዓለም ዙሪያ የተሰሩ ምርምሮች እና ጥናቶችን እንዲሁም የተለያዩ መዛግብትን የያዘውን ግዙፍ ቤተ መጽሐፍት በመጠቀም ጥናት ማድረግ እንዲችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣
* በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ አና እንክብካቤ ትምህርት ላይ በጋራ ለመስራት፣
* በሌላ በኩል በውይይቱ ወቅት የቦንጋ ትምህርት ኮሌጁ በመማር ማስተማር ፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ያከናወናቸው እና እያከናወነ ያለውን ተግባራት ለኤርፈርት ዩኒቨርሲቲ የስራ ኃላፊዎች በአቶ አንተነህ አየለ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።