የቦንጋ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዕጩ መምህራንን በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡
Posted by pimadmin on Saturday, 2 July 2022የቦንጋ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዕጩ መምህራንን በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡
ቦንጋ፣ ሰኔ ፣ 25፣ 2014(ቦመትኮ) የቦንጋ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ 856 ዕጩ መምህራንን በዛሬው ዕለት አስመረቀ
የቦንጋ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ባለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት በመደበኛ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 856 ዕጩ መምህራንን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ኮሌጁ በዛሬው ዕለት በ 20 በተለያዩ የትምህርት መስኮች 473 ወንዶችና 383 ሴት በድምሩ 856 ዕጩ መምህራንን አስመርቋል፡፡
የኮሌጁ ዲን አቶ አንተነህ አየለ ለተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ባስስተላለፉበት ወቅት እንደተናገሩት ኮሌጁ በሰርተፊከት ደረጃ ለማሰልጠን ከተመሰረተበት ጊዜያት አንስቶ በመደበኛና በተከታታይ የስልጠና መረሃ ግብሮች በሰርቲፊኬትና በዲፕሎማ ደረጃ ከ38 ሺ 6መቶ 31በላይ መምህራንን በማሰልጠን ወደ መምህርነት ሙያ ማሰማራቱን ገልፀዋል።
የሀዘን መግለጫ
Posted by pimadmin on Friday, 10 December 2021እጩ ዶ/ር ሙሉብርሃን ሃጎስ አረፈ
ቦንጋ፤ ህዳር 30/2014 ዓ.ም (ቦ/ት/ኮ) እጩ ዶ/ር ሙሉብርሃን ሐጎስ በቦንጋ መ/ራን ትምህርት ኮሌጅ በመ/ርነት ለበርካታ ዓመታት በመ/ርነትና በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች ሲያገለግል የነበረና በስራውም ታታሪ፣ የመልካም ስብዕና ባለቤት፣ ሰው አክባሪና ትሁት የነበረ ሲሆን ላለፉት አራት ዓመታት ለሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከሄደ በኋላም ጭምር ስለ ኮሌጁ እድገትና ለውጥ የሚያስብና በቅርበት የሚከታተል መ/ር ነበር፡፡ በተጨማሪም መ/ሩ በህይወት ዘመኑ ከስራ ባልደረቦቹ፣ ከተማሪዎቹ ጋር፣ ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ከህጻናትና ከልዩ ልዩ የህብረሰተብ ክፍሎች ጋር የነበረው ጤናማ፣ የቀረበ መስተሳሰርና መስተጋብር ለሌሎች አስተማሪና ዘውትር ከህሊና የማይጠፋ ነው፡፡